Isaiah 8

አሦር የእግዚአብሔር መሣሪያ

1 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ትልቅ ሰሌዳ ወስደህ፣ ‘ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ’
በዚህና በቍጥር 3 ላይ፣ ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ ማለት፣ ምርኮ ፈጠነ፤ ብዝበዛ ቸኰለ ማለት ነው።
ብለህ በተለመደው በሰው ፊደል ጻፍበት።
2እኔም፣ ካህኑን ኡሪያንንና የበራክዩን ልጅ ዘካርያስን ታማኝ ምስክሮቼ እንዲሆኑ እጠራቸዋለሁ።”

3እኔም ወደ ነቢዪቱ ሄድሁ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እግዚአብሔርም፣ እንዲህ አለኝ፤ “ስሙን ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ ብለህ ጥራው። 4ሕፃኑም፣ ‘አባባ’ ወይም ‘እማማ’ ብሎ መጥራት ከመቻሉ በፊት፣ የደማስቆ ሀብትና የሰማርያ ምርኮ በአሦር ንጉሥ ይወሰዳል።”

5 እግዚአብሔርም እንደ ገና እንዲህ ሲል ተናገረኝ፤

6“ይህ ሕዝብ በጸጥታ የሚፈስሰውን
የሰሊሆምን ውሆች ትቶ፣
በረአሶንና
በሮሜልዩ ልጅ ተደስቷልና።
7ስለዚህ ጌታ ታላቁንና ብርቱውን
የጐርፍ ውሃ
የኤፍራጥስ ወንዝ ነው።

የአሦርን ንጉሥ ከነግርማ ሞገሱ ሁሉ ያመጣባቸዋል።
ውሃውም ከቦዩ ዐልፎ ተርፎ
በወንዙ ዳር ያለውን ምድር ሁሉ ያጥለቀልቃል፤
8እየጠራረገ ወደ ይሁዳ ይወርዳል፤
እያጥለቀለቀ ያልፋል፤
እስከ ዐንገትም ይደርሳል፤
ዐማኑኤል
ዐማኑኤል ማለት፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።
ሆይ፤
የተዘረጉ ክንፎቹ ምድርህን ከዳር እስከ
ዳር ይሸፍናሉ።”

9እናንተ አሕዛብ፣ ፎክሩ
ወይም፣ የከፋውን ነገር አድርጉ
፤ ነገር ግን ደንግጡ።
በሩቅ አገር ያላችሁ አድምጡ፤
ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤
ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤
10ተመካከሩ፤ ግን አይሳካም፤
ዕቅድ አውጡ፤ ሆኖም አይጸናም፤
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።
ዕብራይስጡ፣ ዐማኑኤል ይላል።

እግዚአብሔርን ፍሩ

11 እግዚአብሔር ብርቱ እጁን በላዬ አድርጎ የእነዚህን ሰዎች መንገድ እንዳልከተል አስጠነቀቀኝ፤ እንዲህም አለኝ፤

12“እነዚህ ሰዎች፣ ‘አድማ’ ብለው የሚጠሩትን፣
ማንኛውንም ነገር፣ ‘አድማ’ አትበሉ፤
ወይም ለስምምነት አትጥሩ፤ እነዚህ ሰዎች ሁልጊዜ ለስምምነት ይጠራሉ

እነርሱ የሚፈሩትን አትፍሩ፤
አትሸበሩለትም።
13ልትቀድሱ የሚገባው የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ብቻ ነው፤
ልትፈሩት የሚገባው እርሱን ነው፤
ልትንቀጠቀጡለት የሚገባውም እርሱ ነው።
14እርሱም መቅደስ ይሆናል፤
ለሁለቱ የእስራኤል ቤት ግን
የሚያደናቅፍ ድንጋይ፣
የሚያሰናክልም ዐለት ይሆንባቸዋል፤
ለኢየሩሳሌም ሕዝብም
ወጥመድና አሽክላ ይሆናል።
15ከእነርሱ ብዙዎች ይሰናከላሉ፤
ይወድቃሉ፤ ይሰበራሉ፤
ወጥመድ ይገባሉ፤ ይያዛሉም።”

16ምስክርነቱን አሽገው፤
ሕጉንም በደቀ መዛሙርቴ መካከል አትመው።
17ፊቱን ከያዕቆብ ቤት የሸሸገውን
እግዚአብሔርን እጠብቃለሁ፤
እርሱንም ተስፋ አደርጋለሁ።
18እነሆ፤ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሰራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ለእስራኤል ምልክትና ድንቅ ነን።

19ሰዎች፣ የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሽኩትን ሟርተኞችንና መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ ቢሏችሁ፣ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕያዋን ምትክ ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ? 20ወደ ሕጉና ወደ ምስክር ቃሉ ሂዱ! እነርሱም እንዲህ ያለውን ቃል ባይናገሩ የንጋት ብርሃን አይበራላቸውም። 21ተጨንቀውና ተርበው በምድሪቱ ላይ ይንከራተታሉ፤ ክፉኛ ሲራቡም ይቈጣሉ፤ ወደ ላይ እየተመለከቱ ንጉሣቸውንና አምላካቸውን ይራገማሉ። 22ከዚያም ወደ ምድር ይመለከታሉ፣ የሚያዩትም ጭንቀት፣ ጨለማና የሚያስፈራም ጭጋግ ብቻ ነው፤ ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይጣላሉ።

Copyright information for AmhNASV